Saturday, 16 June 2012 12:59

“ጥቁር ሰው” የሙዚቃ ክሊፕ ላይ ውይይት ተካሄደ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

አላቲኖስ የፊልም ሰሪዎች ማህበር በቅርቡ የተመረቀውን የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን “ጥቁር ሰው” ቪዲዮ ክሊፕ ለውይይት አቀረበ፡፡ ከትናንት ወዲያ ምሽት በሩስያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል ፑሽኪን አዳራሽ በተከናወነው ውይይት፤ የፊልም ባለሙያዎችና የጥበቡ አፍቃሪዎች ስለፊልም ጥበብ፣ ስለ ክሊፑ ፕሮዳክሽን እና ይዘት እንዲሁም ስለ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ የክሊፑ ረዳት አዘጋጅ ሰው መሆን ይስማው የተገኘ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት ውይይት ራሱ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለመገኘት ቃል መግባቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 1385 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 13:01