በሮያል የማስታወቂያ ድርጅት አዘጋጅነት የሚካሄደውና ራስ መስፍን ስለሺን (አባ ተምትም)ን የሚዘክረው ‹‹ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን›› የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን አርብ ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በአገር ፍቅር ቴአትር ቤት ይካሄዳል፡፡
በእለቱ በእንግድነት የራስ መስፍን ስለሺ ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን በክብር እንግድነት የሚገኙ ሲሆን ሙዚቃ ግጥም ወግና የአርበኛው ሕይወትና ሥራ ታሪክ ለታዳሚ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋዜጠኛና ደራሲ ይጥና ደምሴና በጋዜጠኛ ኢዮብ አባተ አስተባባሪነት በሚካሄደው ኪነ ጥበባዊ መሰናዶው ድምፃዊት መሰረት በለጠ፣ በቀለ አረጋ፣ አብነት ደምሴ የክራር ባለሙያዋ የትናየት ይልማ ፍሬዘር ኩራባቸውና ማፊ ልዑል በኢስት አፍሪካ ባንድ ታጅበው የሚያቀነቅኑ ሲሆን፣ ገጣሚያኑ አስታውሰኝ ረጋሳና ትርሲት ሃብተማሪያም ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ መድረክ መሪው አንጋፋው ጋዜጠኛ አባተ ማንደፍሮ ሲሆን መግቢያው ነፃ ነው ተብሏል፡፡
Saturday, 02 November 2019 12:48
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና