Print this page
Saturday, 02 November 2019 12:37

‹‹ለነጋችን ተስፋ ለሰላም እንልፋ›› የኪነ ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን የሚዘጋጀው ወርሃዊ የኪነ ጥበብ ምሽት የዚህ ወር ፕሮግራም ‹‹ለነጋችን ተስፋ ለሰላም እንልፋ›› በሚል መሪ ቃል ከነገ በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) እና መምህር ዘመዱ ደምስስ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን፤ በገጣሚና ተወዛዋዥ ኤፍሬም መኮንን (ኤፌማክ) እና ተስፋሁን ከበደ ግጥም በውዛዋዜ፣ ተዋናይ ሄኖክ በሪሁን መነባንብ፣ በላይ በቀለ ወያ ግጥም አርቲስት ፍቃዱ ከበደና ዘሪሁን ሙላት ቴአትር እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡
በምሽቱ ለመታደም የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ሲሆን ትኬቶቹ በጃፋር፣ በአይናለም እና በዮናስ መጽሐፍት መደብሮች፣ በጣይቱ ሆቴል፣ ካዛንቺስ በሚገኘው በጆሲ ልብስ ስፌት ቤትና በአቻሬ ጫማ መደብር እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

Read 1113 times