Saturday, 02 November 2019 12:41

የአማራ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ውይይት ዛሬ ይጀመራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   በአማራ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት የሚካሄደው የአማራ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ውይይት ዛሬ በባህር ዳር ይጀመራል፡፡
የአማራ ተወላጅ የሆኑ ከያንያን ማለትም ደራሲያን፣ የቴአትር ባለሙያዎች፣ ፊልም ሰሪዎች፣ ገጣሚዎችና በማንኛውም ኪነ ጥበብ ሙያ ላይ ያሉ የሚሳተፉበት ነው በተባለው በዚህ ውይይት ላይ ዛሬ ሶስት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን ጽሑፎቹ የክልሉ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ብሎም ለክልሉ እድገትና ብልጽግና ምን እያደረጉ እንደሆነ ወደፊት ምን ማድረግ እንደሚገባቸውና እስካሁን የሰሯቸው ስራዎች ስኬትና ውድቀት ላይ እንደሚያተኩሩ ለማወቅ ችለናል፡፡
በነገው ዕለት እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ተሳታፊዎቹ የተለያዩ ታሪካዊ፣ የቱሪስት መስህብ የሆኑ ቦታዎችንና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሚጎበኙ ሲሆን በዚሁ ዕለት ምሽት የዕውቅናና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ተከናውኖ መርሃ ግብሩ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡


Read 8209 times