Saturday, 16 June 2012 12:45

የወጣቷ የሥዕል አውደርዕይ በጣይቱ እየታየ ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

በወጣት ሰዓሊ ሜላት አክሊሉ የተዘጋጀው የሥዕል አውደርዕይ ከሰኔ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በጣይቱ ሆቴል ለተመልካች እንደቀረበ ተገለፀ፡፡ በመጪው ማክሰኞ ይዘጋል ተብሎ የሚገመተው አውደርዕይ፤ ለተጨማሪ ቀናት እንዲታይ ጥረት እያደረገች መሆኗን ሰዓሊዋ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፃለች፡፡የስዕል አውደርዕይ በግሏ ስታቀርብ የመጀመርያዋ የሆነችው ሜላት፤ ሥራዎችዋ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ፣ በጐተ የጀርመን ባህል ተቋምና በገብረክርስቶስ ደስታ ማዕከል እንደሚገኙና ካሁን ቀደም ከሌሎች ሰዓሊዎች ጋር መሰል አውደርዕይ እንዳቀረበች ገልፃለች፡፡

 

 

Read 800 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 12:52