Saturday, 19 October 2019 12:34

ሆሄ የሥነጽሁፍ የሽልማት ሥነሥርዓት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ሆሄ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት ለሶስተኛ ጊዜ፣ በአምስት ዘርፎች የተካሄደውን ውድድር፣ የመጨረሻ ውጤት ይፋ በማድረግ፣ አሸናፊዎችን የሚሸልምበት ሥነሥርዓት የፊታችን ማክሰኞ፣ ከቀኑ 12:00 ጀምሮ  በብሔራዊ ቴአትር  ያካሂዳል። የሆሄ ሽልማት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም እንደገለፁት፤ ቀድሞ በሶስት ዘርፍ ይካሄድ የነበረው የሥነጽሑፍ ሽልማቱ፤ (ረዥም ልቦድ፣ ግጥምና የህፃናት ዘርፍ፣ እንዲሁም የሳይንስና ምርምር መጻሕፍትና የትግርኛና የኦሮምኛ መጻሕፍትን ለውድድር አቅርቧል።
 ባለፉት ጥቂት ሳምንታት፣ ከየዘርፉ አምስቱ ምርጦች ለህዝብ ይፋ ተደርገው፣ ድምፅ እየተሰጠባቸው ሲሆን ከየዘርፉ የመጨረሻዎቹ አሸናፊዎች ማክሰኞ ይታወቃሉ፡፡
በሥነሥርዓቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች፣ የመንግስት ሃላፊዎችና የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች የሚታደሙ ሲሆኑ የሽልማት ድርጅቱ አጋር ኢቢኤስ ቴሌቪዥን፣ፕሮግራሙን በቀጥታ ያስተላልፋል ተብሏል፡፡

Read 1113 times