Print this page
Saturday, 19 October 2019 12:40

6ኛ ህያው የኪነ - ጥበብ ጉዞ ሰኞ ይጠናቀቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


             በኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው 6ኛው ሕያው የኪነ-ጥበብ ጉዞ ወደ ታሪካዊቷ ሸዋ” ሰኞ ይጠናቀቃል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ጥቅምት 5 ቀን 2012 ከማህበሩ ዋና ጽ/ቤት በቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) የተጀመረው ይሄ ጉዞ የኢትዮጵያ አባት የሆኑት እምዬ ምኒልክ በታሪክ አሻራቸው ጐልቶ የሚታየውን መጽሐፍ ደራሲ ዳኛቸው ወርቁ፣ የአርበኛዋ ሸዋረገድ ገድሌ፣ የፀሐፊ ትዕዛዝ ዲፕሎማትና ጠ/ሚ አክሊሉ ሃብተወልድ፣ የፊደል አባት ተስፋ ገ/ስላሴ ዘብሔረ ቡልጋ፣ የአርቲስት ወጋየሁ ንጋቱ፣ የሌሎችም ታላላቅ ሰዎች የትውልድ ቦታና ታሪካቸውን እየዘከረ ይገኛል::
26 የኪነጥበብ ማህበራት፣ በርካታ የብዙሃን መገናኛዎች፣ ገጣምያን፣ ደራስያንና ታዋቂ ሰዎች በጉዞው የተካተቱ ሲሆን፤ ባለፉት ዓመታት መሠል ኪነጥበባዊ ጉዞዎች ተካሂደዋል፡፡ የጉዞው መደምደሚያም የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚሆን የደራስያን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበረ አዳሙ ተናግረዋል፡፡


Read 6974 times