Saturday, 19 October 2019 12:14

በዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሚመራው ‹‹ትዴት›› ዛሬ በሀገር ፍቅር ቲያትር ህዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 በዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሚመራው የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) በዛሬው እለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት አዳራሽ ህዝባዊ ውይይት እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
ለረጅም አመታት በውጭ ሀገር ሆኖ ሲንቀሳቀስ የቆየውና ለውጡን ተከትሎ ከአመት በፊት ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ‹‹ትዴት››፤ በወቅታዊ የሀገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረውን የመጀመሪያውን ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግ የፓርቲው ሊቀ መንበር ዶ/ር አረጋዊ በርኼ፤  ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡
በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ለውጥ በስፋት የሚገመገም ሲሆን ለውጡ በትግራይ ላይ ያለውን አንድምታ እንዲሁም በትግራይ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ዶ/ር አረጋዊ አስታውቀዋል፡፡
ህወኃት በቅርቡ የያዘውን የፖለቲካ አቋምና መግለጫዎቹ እንዲሁም የህወኃትና የትግራይ ህዝብን ግንኙነት በተመለከተም በስፋት ውይይት ይደረግበታል ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት ተሳትፈው እንዲመክሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read 7395 times