“ማዳጋስካር 3” ምርጥ የቤተሰብ ፊልም መሆኑን የጠቆመው ሎስአንጀለስ ታይምስ፤ ፊልሙ በ145ሚ.ዶላር በጀት እንደተሰራ አመልክቷል፡፡ በፊልሙ ላይ ቤን ስቴለር፤ ክሪስ ሮክ፤ ጃዳ ፒንኬት ስሚዝ እና ዴቪድ ስኩዊመር በድምጽ ሲተውኑ እስከ 5ሚ.ዶላ እንደተከፈላቸው ታውቋል፡፡ፊልሙ በአጠቃላይ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሊያስገኝ እንደሚችልም ተገምቷል፡፡ ከሰባት ዓመት በፊት በ78 ሚሊዮን ዶላር የተሰራው የፊልሙ የመጀመርያው ክፍል 532.68 ሚሊዮን ዶላር ሲያስገባ፤ ከአራት ዓመት በፊት በ150 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራው ሁለተኛው ክፍል 604 ሚሊዮን ዶላር አስገብቷል፡፡