Print this page
Saturday, 16 June 2012 12:40

ሮድ ስትዋርት ሁለት አልበሞችን እየሰራ ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

የሮክ ሙዚቃ አቀንቃኙ ሮድ ስትዋርት በሁለት አዳዲስ አልበሞች ስራ እንደተወጠረ የጠቆመው ኒውዮርክ ፖስት፤ አልበሞቹ በ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት ዋዜማ እንደሚለቀቁ ዘግቧል፡፡ አርቲስቱ ከአልበም ሥራዎቹ ጐን ለጐን በመጪው ሀምሌ ወር በአሜሪካ ለሚያቀርባቸው የሙዚቃ ኮንሰርቶች ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ዴይሊሜል ዘግቧል፡፡  የ67 ዓመቱ ሮድ ስትዋርት ከዚህ በተጨማሪም “ኔቨር ኤ ደል ሞመንት” በሚል ርእስ የህይወት ታሪኩን በመፅሃፍ አሳትሞ ሊያወጣ መሆኑን አመልክቷል፡፡ በመጪው አዲስ ዓመት ለአድማጭ ከሚያቀርባቸው ሁለት አልበሞች አንደኛው ከታዋቂው ካናዳዊ አርቲስት ማይክል ቡብሊ ጋር የሰራቸው ዘፈኖች የሚገኙበት የክሪስማስ አልበም መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው ሌላኛው አልበም በራሱ ለስላሳ የሮክ ሙዚቃ ስልት የተሰሩ ዘፈኖችን ማካተቱን ገልጿል፡፡

ሮደሪክ ዴቪድ ሮድ ስትዋርት በሚል ስሙ የሚጠራው የሮክ ሙዚቃ ኮከቡ፤ ባለፈው ዓመት “ሰንደይ ታይምስ” ይፋ ባደረገው የብሪትሽ ሃብታም አርቲስቶች ደረጃ፣ ከ20ዎቹ ተርታ መሰለፍ ችሏል - 115 ሚሊዮን ዶላር ሃብት በማስመዝገብ፡፡ አርቲስቱ በሙያው በቆየባቸው 48 ዓመታት አሥር አልበሞችን ያወጣ ሲሆን በመላው ዓለም ከ100 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎችን እንደሸጠ ታውቋል፡፡

 

 

Read 716 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 12:43