Saturday, 12 October 2019 11:57

“‘የፖለቲካ እስረኞችን’ ለማስፈታት መንግስትን እከሳለሁ”

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 “በፖለቲካና በብሔር ምክንያት የታሠረ የለም” - መንግስት

       አለማቀፍ የትግራይ ተወላጆች ንቅናቄ››፤ “የፖለቲካ እስረኞች ናቸው” ያላቸውን የትግራይ ተወላጅ እስረኞች ለማስፈታት፣ 20ሺህ ፊርማ አሰባስቦ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ክስ ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር በሙስና ጠርጥሮ ያሠራቸው የቀድሞ የሜቴክ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የትግራይ ተወላጆች የእስር ምክንያት ‹‹ፖለቲካ” ነው› ብሎ እንደሚያምን በሰጠው መግለጫ ጠቁሟል ንቅናቄው፡፡
እነዚህን እስረኞች ለማስፈታትም የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለፀው ንቅናቄው፤ በአንድ ሣምንት ውስጥ 20ሺህ ፊርማ በማሰባሰብ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አቅርቦ፣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል::
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ ‹‹ህግ በማስከበር ሂደት ውስጥ በፖለቲካና በብሔር ምክንያት ክስ የተመሠረተበት የትግራይ ተወላጅ የለም›› ሲል አስተባብሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ በጥር 2019 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርቱ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው የነበሩ የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸው መልካም እርምጃ መሆኑን በአድናቆት መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡  


Read 7715 times