Print this page
Saturday, 12 October 2019 11:56

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የጠየቀው የ3.8 ሚ. ብር ባጀት ተቀባይነት አላገኘም

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

  ‹‹ይህን ያህል በጀት ለመመደብ አቅም የለኝም›› ምርጫ ቦርድ
     የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ለ3 ወር የጠየቀው የ3.8 ሚ.ብር ባጀት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ምክንያት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ አለመሆኑን አስታወቀ፡፡
ኢህአዴግን ጨምሮ ከ107 በላይ ፓርቲዎች የቃልኪዳን ሰነድ ተፈራርመው የመሠረቱት የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፤ ለ3 ወራት ስራ ማስኬጃ የጠየቀው የ3.8 ሚሊዮን ብር ባጀት ተቀባይነት አላገኘም ምርጫ ቦርድን ይሄን ያህል በጀት ለመመደብ አቅም የለኝም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በዚሁ ጉዳይ ላይ ለአዲስ አድማስ ማብራሪያ የሰጡት የጋራ ም/ቤቱ ም/ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ፣ ም/ቤቱ ለረጅም ጊዜ የበጀት ጥያቄውን ሲያቀርብ መቆየቱንና እስካሁን በጐ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጸዋል፡፡
ለ3 ወር የተጠየቀው የ3.8 ሚሊዮን ብር ባጀት ጽ/ቤቱን ለማደራጀት፣ በአባላት መካከል የተፈጠሩ ቅሬታዎችን ለማጣራት እንዲሁም ስልጠናዎችና ውይይቶችን ለማዘጋጀት የሚውል መሆኑን የም/ቤቱ ሰብሳቢ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡
በጀቱን መፍቀድ ያለበት ምርጫ ቦርድ መስከረም 21 ቀን 2012 ዓ.ም ለጋራ ም/ቤቱ በፃፈው ደብዳቤ፤ የተጠየቀውን በጀት መስጠት እንደማይችል መግለፁንና በቀጣይ ቀናት በጉዳዩ ላይ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ፣ ም/ቤቱ ከበጀት ጋር የተያያዘ አቤቱታውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤ ምላሻቸውን እየተጠባበቀ ነው ተብሏል፡፡  

Read 6783 times