Saturday, 05 October 2019 00:00

“አማር ORO” የግጥም መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በገጣሚ መስቀሉ ባልቻ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋ የተፃፉ በርካታ ግጥሞችን የያዘው ‹‹አማር ORO›› የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
በፖለቲካዊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በአገር ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ግጥሞችን ያካተተው መጽሐፉ፣ አርትኦቱ በየሻው ተሰማ (የኮተቤው) መሠራቱ ታውቋል፡፡ በ224 ገፆች የተዘጋጀው “አማር ORO”፤ በ200 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡


Read 9707 times