Saturday, 05 October 2019 00:00

የትንሳኤ ኪነ-ጥበብ ሁለተኛው ምሽት አርብ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


              በሳሚ ህትመትና ማስታወቂያ ድርጅት በየወሩ የሚካሄደው ‹‹ትንሳኤ ኪነ-ጥበብ ምሽት›› ሁለተኛው ዙር አርብ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ11፡00 ጀምሮ ሰሜን ማዘጋጃ በሚገኘው ሳሬም ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሄዳል። በዕለቱ ግጥም፣ ወግ፣ ዲስኩር፣ መነባንብ ሙዚቃና ስታንዳፕ ኮሜዲ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን ታዋቂ ሰዎች ለስኬት ያበቋቸውን ሰዎች መርጠው በማቅረብ በዕለቱ ልዩ ሽልማት እንዲያገኙ ያደርጋሉም ተብሏል፡፡
በዚህ ምሽት አርቲስት መላኩ አለማየሁ፣ አርቲስት ሞገስ ወ/ዮሐንስ፣ ገጣሚ ትርሲት ሃ/ማሪያም፣ ጋዜጠኛ አሸብር በቀለ፣ አርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኮሜዲያን አሰፋ ተገኝና ሌሎችም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን እውቋ የክራር ተጫዋች የትናየት ይልማ በክራር እንደምታጅባቸው የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሳሙኤል ንጉሴ አስታውቋል፡፡

Read 899 times