እናት የማስታወቂያ ድርጅት ከጎተ ኢንስቲትዩትና ከወዘመክር ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ‹‹ለወገንና ለአገር ክብር፣ ሜጀር ጀነራል መርዕድ ንጉሴ እና ኢትዮጵያ›› በተሰኘውና በሜጀር ጀነራል መርዕድ ንጉሴ የውትድርና ሕይወትና ሥራ ላይ በሚያተኩረው መጽሐፍ ላይ በኢትዮጵያ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የፍልስፍና ምሁሩ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ አዘጋጁ ጋብዟል፡፡