Saturday, 05 October 2019 00:00

‹ለአገር ፈውስ የጥላቻን አጥር ማፍረስ›› የኪነ ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

‹በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚቀርበው ‹‹በአገር ፈውስ የጥላቻን አጥር ማፍረስ›› የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ሰኞ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕለቱም ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደና መምህር ዮናስ ዘውዴ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን፣ አርቲስት አንዷለም አባተ (የአፀደ ልጅ) የአቡነ ጴጥሮስን ቴአትር በመነባነብ መልክ ያቀርባል ተብሏል፡፡ መምህርት እፀገነት ከበደ፣ ዶ/ር አብዱላዚዝ ዲኖ፣ ወግ የሚያቀርቡ ሲሆን መላኩ ታረቀኝ ፉከራ ያቀርባል ተብሏል፡፡
በዚህ ዝግጅት ለመታደም የመግቢያው ዋጋ 100 ብር ሲሆን ትኬቶቹን በጀፋር መጽሐፍ መደብር፣ በአይናለም መጽሐፍ መደብር፣ በዮናስ መጽሐፍት መደብር፤ ጣይቱ ሆቴል፣ ካዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት፣ በአቻሬ ጫማና አራት ኪሎ በሚገኘው ማዮን መጻሕፍት መደብር ማግኘት እንደሚቻል አዘጋጁ ገልጿል፡፡

Read 861 times