Saturday, 16 June 2012 12:37

ሪሃና በአሳሳቢ የጤና ሁኔታ ላይ ናት

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

ከወር በፊት በአቅም መዳከምና በድርቀት ታምማ ሆስፒታል የገባችው ሪሃና፤ አሁንም በአሳሳቢ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ፡ ሰሞኑን በእንግሊዝ ለ10 ሳምንታት የነበራትን ቆይታ የሰረዘችው የ24 አመቷ በርባዶሳዊት ያለችበት ችግር የዊትኒ ሃውስተንን አሳዛኝ መጨረሻ የሚያስታውስ እንዳይሆን ተሰግቷል፡፡ የቅርብ ወዳጇ የሆነው ጄይ ዚ  ጊዜው ሳይዘገይ በፊት የህክምና እርዳታ እንድታገኝ እንደመከራትም ተወርቷል፡፡ ዘንድሮ እጅግ እርቃን በሚያሳዩ አለባበሶች በተደጋጋሚ የታየችው ሪሃና፤  ከልክ ያለፈ ጭፈራ እና መዝናናት ማብዛቷ ለጤናዋ መቃወስ ሰበብ እንደሆነባት አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በየሳምንቱ ለፀጉሯ ብቻ 14ሺ ዶላር ታወጣለች የምትባለው ሪሃና፤ በዓመት ውስጥ ለውበቷ መጠበቂያ እስከ 850ሺ ዶላር ወጭ እያደረገች ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ አርቲስቷ ከዚህ ቀደም ድብደባ ፈጽሞባታል ከተባለው የቀድሞ  ፍቅረኛዋ ክሪስ ብራውን ጋር የፍቅር ግንኙነት በድብቅ መጀመሯ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ ሁለቱ አርቲስቶች ሰሞኑን በአንድ መዝናኛ ውስጥ አንድ ላይ መታየታቸውን ያመለከቱ መረጃዎች፤  ክሪስ ከአክስቷ ልጆችና ከአያቷ ጋር ሲዝናና በተደጋጋሚ መታየቱም ተጠቁሟል፡፡ ሪሃና በቅርቡ በሰጠችው ቃለምልልስ “የምኖረው ለራሴና ለፈጣሪዬ ብቻ ነው” ማለቱ ይታወቃል፡

 

Read 2148 times