Print this page
Tuesday, 01 October 2019 10:13

‹‹ጤና ይስጥልን›› ወርሃዊ መጽሔት መታተም ጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የሕክምና ባለሙያዎች በስፋት የሚሳተፉበትና በጤና ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ‹‹ጤና ይስጥልን›› የተባለ ወርሃዊ መጽሔት መታተም ጀመረ፡፡
በዶ/ር ሰላም አክሊሉ ማኔጂንግ ዳይሬክተርነት እየታተመ ለንባብ በሚበቃው በዚህ መጽሔት ላይ ሃኪሞች፣ የኒውትሪሽን ባለሙያዎችና ከጤና ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ሙያተኞች ይሳተፉበታል ተብሏል።
የመጽሔቱ አሳታሚዎች ትናንት በፎያት ሆቴል ባዘጋጁት የመጽሔቱ የትውውቅ ፕሮግራም ላይ ዶ/ር ሰላም አክሊሉ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት በአገራችን እጅግ ከፍተኛ በሆነ መጠን ሕብረተሰቡን ለጉዳት እያጋለጡ ያሉት የማይተላለፉ በሽታዎች መሆናቸውን ጠቁመው፣ ሕብረተሰቡ ስለነዚህ በሽታዎች ምንነትና በበሽታዎቹ ላለመያዝ ማድረግ ስለሚገባው ቅድመ ጥንቃቄ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚረዳና በባለሙያዎች የሚዘጋጅ መጽሔት ነው ብለዋል፡፡ መጽሔቱን አነስተኛ በሆነ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ የተነሳሱትም ሕብረተሰቡ በቀላሉ ስለ ጤናው እንዲያውቅና ራሱን ከበሽታ እንዲጠብቅ ለማስቻል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

Read 985 times