Saturday, 21 September 2019 12:38

46ሺ ጥይትና 497 ሽጉጥ ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል ተያዘ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 በነዳጅ በጫነ ቦቴ ውስጥ ተደብቆ ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ 46ሺ ጥይትና 497 ሽጉጥ አማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ ተይዟል፡፡
በሃያ ጆንያዎች ተቋጥሮ በነዳጅ ቦቴ ውስጥ የተደበቀውና ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል የተያዘው ይኸው የጦር መሳሪያ፤ ከመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ክትትልና ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ መሰረት መያዙን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ባህርዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ውስጥ የተያዘው ነዳጅ የጫነ ቦቴ በውስጡ የጫናቸውን 46ሺህ ጥይቶችና 497 ሽጉጦች ይዞ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ እንደነበርም መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ የነዳጅ ቦቴው በተያዘበት ወቅት አሽከርካሪው ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም በፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር መዋሉም ታውቋል፡፡

Read 1592 times