Tuesday, 17 September 2019 00:00

የዘጠነኛው ዙር ‹‹ለዛ ሽልማት›› ምርጥ ስድስት ዕጩዎች ታወቁ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በየዓመቱ የተመረጡ የኪነ ጥበብ ውጤቶችንና ሙያተኞችን የሚሸልመው ‹‹ለዛ ሽልማት››፣ ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ ስድስት የኪነ ጥበብ ሥራዎችንና ሙያተኞችን ከየዘርፉ መርጦ ይፋ አደረገ፡፡ በዘንድሮ ‹‹የአመቱ ምርጥ አልበም›› ዘርፍ የጃሉድ አወል ‹‹ንጉስ››፣ የጎሳዬ ተስፋዬ ‹‹ሲያምሽ ያመኛል››፣ የቸሊና ‹‹ቸሊና›› የበሀይሉ ታፈሰ (ዚጊዛጋ) ‹‹ኮርማ››፣ የጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ‹‹ባላምባራስ›› ሲመረጡ፣ በ‹‹የአመቱ አዲስ ዘፋኝ›› ዘርፍ፡- ቸሊና፣ በሀይሉ ታፈሰ (ዚጊዛጋ)፣ ዮሃና፣ ሀይለየሱስ ፈይሳና ዳግ ዳንኤል ምርጥ ስድስት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ‹‹የአመቱ ነጠላ ዜማ ዘርፍ›› ውስጥ የራሄል ጌቱ ‹‹ጥሎብኝ››፣ የጃምቦ ጆቴ ‹‹ቢልባ››፣ የዳጊ ማኛ ‹‹ማሂያ››፣ የአብርሃም በላይነህ ‹‹እቴ አባይ››፣ የያሬድ ነጉ ‹‹አዲመራ›› እና የኤፍሬም አማረ ‹‹አሰይ›› መመረጣቸው ታውቋል፡፡ በዓመቱ ተከታታይ የቴሌቪዥን ፊልሞች ዘርፍ ደግሞ የፋናው ‹‹ደርሶ መልስ››፣ የኢቢኤስ ‹‹ሞጋቾች››፣ የፋናው ‹‹ዘጠነኛው ሺህ››፣ የኢቲቪው ‹‹ቤቶች››፣ የፋናው ‹‹ምን ልታዘዝ›› እና የኢቢኤስ ‹‹ዘመን›› ሲመረጡ፤ በ‹‹ምርጥ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ተዋንያን›› ዘርፍ፡- ሃና ዮሐንስ ከ‹‹ዘመን››፣ መስከረም አበራ ከ‹‹ምን ልታዘዝ››፣ መቅደስ ፀጋዬ ከ‹‹ሞጋቾች››፣ ክርስቲ ሀይሌ ከ‹‹ደርሶ መልስ››፣ መስታወት አራጋው ‹‹ከሰንሰለት›› እና ማርታ ጌታቸው ‹‹ከደርሶ መልስ›› ወደ ምርጥ ስድስት  አልፈዋል፡፡
በለዛ ሽልማት አዘጋጆች ገለጻ መሰረት፤ ከዓመቱ ምርጥ ፊልሞች መካከል ‹‹ተፈጣሪ››፣ ‹‹ቁራኛዬ››፣ ‹‹ዘመኔ››፣ ‹‹ወደፊት›› ‹‹ሞኙ ያራዳ ልጅ›› እና ‹‹ሲመት›› ወደ ምርጥ ስድስት እጩዎች አልፈዋል፡፡ በ‹‹የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ›› ዘርፍ፡- ዘሪሁን ሙላት፣ በ‹‹ቁራኛዬ››፣ ግሩም ኤርሚያስ፣ በ‹‹ተፈጣሪ››፣ ሄኖክ ወንድሙ፣ በ‹‹ሱማሌው ቫንዳም››፣ ታሪኩ ብርሃኑ፣ በ‹‹ሞኙ ያራዳ ልጅ››፣ ዓለም ሰገድ ተስፋዬ በ‹‹አትፍረድ›› እና ቸርነት ፍቃዱ በ‹‹ዘመኔ›› ሲመረጡ፤ በ‹‹የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት›› ዘርፍም፡- ሜላት ይርጋለም በ‹‹በራብሽ››፣ ዕድለወርቅ ጣሰው በ‹‹ወደፊት፣ የምስራች ግርማ በ‹‹ቁራኛዬ››፣ መስከረም አበራ በ‹‹ሲመት››፣ ቃል ኪዳን ጥበቡ በ‹‹ዘመኔ›› እና ሸዊት ከበደ በ‹‹ውሃና ወርቅ›› ተመርጠዋል፡፡ በ‹‹የአመቱ ምርጥ ዘፈን›› ዘርፍም የበሀይሉ ታፈሰ (ዚጊዛጋ) ‹‹ሰርካለሜ››፣ የቸሊና ‹‹ባቲ››፣ የዮሃና ‹‹ማይ ላጃ››፣ የበሃይሉ ታፈሰ (ዚጊዛጋ) ‹‹ጉም ሰማይ››፣ የዳግ ዳንኤል ‹‹ሀበሻ›› እና የጎሳዬ ተስፋዬ ‹‹ሰላም ይስጠን›› ተመርጠዋል።
የመጨረሻው ዙር የውድድሩ አሸናፊዎች በጥቅምት አጋማሽ ላይ በሚካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደሚታወቁና እንደሚሸለሙ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ ገልጿል፡፡  

Read 1746 times