Saturday, 14 September 2019 10:49

ኢዜማ ነገ በመቐሌ ህዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

  የኢትዮጵያ ዜጐች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ ህዝባዊ ስብሰባውን  ነገ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመቐሌ ያካሂዳል፡፡
ህዝባዊ ስብሰባውን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋና የፓርቲው ም/መሪ አንዱዓለም አራጌ የሚመሩት ሲሆን ስብሰባውም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በመቐሌ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ እንደሚካሄድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ናትናኤል ፈለቀ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የፓርቲውን አላማና ግብ፣ ፕሮግራሙንና አጀንዳውን በስፋት ለህዝብ እንደሚያስተዋውቅ የገለፁት አቶ ናትናኤል፤ ከህዝቡ ለሚነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ይሰጥበታል ብለዋል፡፡
ኢዜማ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የተመረጡ ከተሞች ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን በተከታታይ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡


Read 6488 times