Print this page
Saturday, 14 September 2019 10:45

‹‹ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእሬቻ በዓል ላይ እንዲገኝ ጥሪ አስተላልፋለሁ››

Written by  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር፤ ሽመልስ አብዲሳ)
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ እድል አግኝቷል፤ ይሄን እድል በአግባቡ ካልተጠቀመ ትልቅ ኪሳራ ነው የሚሆነው:: አገሪቱ ከፍተኛ ችግር ላይ ትወድቃለች:: ብዙ አገሮች እንደዚህ አይነት እድሎችን ባለመጠቀማቸው፣ የለውጥ እቅድ ተጨናግፎ፣ ብዙ ጥፋቶች ደርሰዋል፡፡ አገራቸው የማትወጣበት ማጥ ውስጥ ተዘፍቃ ኑሮ መከራ የሆነባቸው ብዙ አገሮችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
በአገራችንም ብዙ ለውጦች ከሽፈዋል፡፡ አሁን ያገኘነው ለውጥ ግን ከፍተኛ ውጤት የተገኘበት ነው:: ወደ ኋላ አንድ አመት ተኩል ተመልሰን ብናስታውስ፤ አስገራሚ የሆነ ለውጥ ተካሄዷል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለውጡን ማስቀጠል ይገባዋል:: ሁላችንም፤ መንግስትም ሕዝብም ተባብረን በአንድ ላይ ይሄንን ለውጥ ማስቀጠል ከቻልን፣ የምንናፍቃትን ኢትዮጵያን እንፈጥራታለን፡፡ ሁሉንም እኩል የምታከብር፣ ብሔር ብሔረሰብ እኩል የሚከበርባት፣ ሁሉም የሚተሳሰብባት፣ ወንድማማችነት የሚጠነክርባት አገር መፍጠር እንችላለን፡፡ እኔን እንቅልፍ የሚነሳኝ ይሄንን እድል እየተጠቀምንበት ነው አይደለም? በየቀኑ ለውጡን የሚያስቀጥል ሥራ እያከናወንን ነው አይደለም? የሚለው ነው፡፡ ተግዳሮቶችን በትዕግስትና ከስሜት በፀዳ አስተሳሰብ እየተጋፈጥን ከሄድን፣ ነገሮች በፍጥነት ይቀየራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ለውጥ አለም እየመሰከረ እንዳለው ሁሉ፣ በተግባር የምናየው ይሆናል። ለውጥ አሁን ላለው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለመጪውም ትውልድ የምናሻግረውና የምናቀብለው ነው፡፡ ስህተቶችን እያረምን፣ አዳዲስ አስተሳሰቦችን በመቅረጽ ወደፊት መጓዝ አለብን፡፡
አዲሱ አመት የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ በዘንድሮ የእሬቻ በአል ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተገኝቶ እንዲያከብር ጥሪ አስተላልፋለሁ:: እሬቻ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብና የእኩልነት በአል ነው፡። በደስታ የሚከበር በዓል ነው፡፡                   

Read 1235 times