Saturday, 07 September 2019 00:00

“የመስዋዕትነት አሻራ” ባለፈው ቅዳሜ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የብ/ጀነራል ከበደ ጋሼ “የመስዋዕትነት አሻራ” የተሰኘ መጽሐፍ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ በራስ ሆቴል ገበታ አዳራሽ ተመረቀ፡፡ መጽሐፉ የብ/ጀነራል
ከበደ ጋሼን ከልጅ ወታደርነት እስከ ጀነራልነት የዘለቀ የአርባ አመታት የውትድርና ህይወት ይተርካል ተብሏል፡፡
በርካታ ታሪካዊ ፎቶግራፎችን ያካተተው መጽሐፉ፤ በ310 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ150 ብር፣ በ20 ዶላርና በ20 ዩሮ ለገበያ ቀርቧል፡፡ በምርቃት
ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመጽሐፉ ዳሰሳን ጨምሮ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች መቅረባቸውም ታውቋል፡፡


Read 10325 times