Saturday, 07 September 2019 00:00

አቢሲኒያ ሽልማት የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

አቢሲኒያ ሽልማት ‹‹አለምንና ሕዝቦቿን የሚታደግ ስራ ለሰሩ ትጉሃን እንሸልማለን›› በሚል መርህ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የ2011 ዓ.ም ሽልማት የፊታችን ሰኞ በሁለት ፈረቃዎች የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ልዩ ተሸላሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ናቸው ተብሏል፡፡ በአፍሪካ ደረጃ ደግሞ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እንደሚሸለሙ የሽልማት ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በአገራችን በአፍሪካና በአለም ከፍተኛ ስራ ለሰሩ ትጉሃን በ778 መስኮች ሽልማትን ሲሰጥ የነበረው ድርጅቱ፤ ዘንድሮም በኦሮሞ ባህል ማዕከል ከቀኑ 8፡30 - 12፡00 በሚካሄድ ስነ ሥርዓት በከፍተኛ በሁለተኛ፣ በሶስተኛና በአራተኛ ደረጃ ከፋፍሎ የሚሸልም ሲሆን በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈው ጀነራል ሰዓረ መኮንን፣ አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/መድህን፣ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናና ሌሎች 37 ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች በሽልማቱ እንደሚካተቱ ታውቋል፡፡

Read 1909 times