Saturday, 07 September 2019 00:00

‹‹ወርቃማው ጉዞ›› የባህልና የኪነ ጥበብ ጉዞ ተጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ናብሊስ ኮሙዩኒኬሽንና ተጉለት ሚዲያና ፕሮሞሽን ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጋር በትብብር የሚያዘጋጁት ‹‹ወርቃማው ጉዞ›› የተሰኘ የባህል፣ የኪነ ጥበብና የቱሪዝም ጉዞ በይፋ ተጀመረ፡፡ ይህ አነቃቂ ጉዞ በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ኪነ ጥበቦችን፣ የቱሪዝምና ባህላዊ ትውፊቶችን መዳረሻው አድርጎ የሚካሄድ ሲሆን በዓመት 12 ጉዞዎችን ለማድረግ የታቀደ ነው ተብሏል፡፡
የመጀመሪያው ጉዞውን ባለፈው ሳምንት በአፄ ምኒልክ መናገሻ አንኮበር በማድረግ፣ በርካታ የአካባቢውን ባህል፣ ታሪክና ኪነ ጥበብ ለሌላው ማህበረሰብና ለመላው አለም የሚያስተዋውቅ ተግባር አከናውኖ መመለሱን አዘጋጆቹ በዚህ ሳምንት አጋማሽ በጣይቱ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ይህን ጉዞ መለያ (ብራንድ) ለማድረግ አዘጋጆቹ ጥረት ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ወደ ሀረር፣ አርባ ምንጭ፣ ደሴ ሀይቅ፣ እስጢፋኖስ፣ ጎንደርና ባህር ዳር ጉዞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሆኑም  ታውቋል።
የጉዞው ዋና ዓላማ፤ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን የማወቅና የመጎብኘት ልምድ እንዲያዳብሩ ለማድረግ ሲሆን ጉዞው የበላይ ጠባቂ፣ የሚዲያና የቱሪዝም አማካሪዎችና የቱሪዝም መዳረሻ ተጠሪዎችም አሉት ተብሏል፡፡

Read 805 times