Saturday, 07 September 2019 00:00

አድማስ ዩኒቨርስቲ ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤውን ዛሬ ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በጉባኤው ከ6-8 የሚደርሱ ጥናታዊ ጽሑፎች ይቀርባሉ

          የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ጥናትና ምርምሮች ላይ ትኩረት አድርጎ በየአመቱ የጥናትና ምርምር ጉባኤ የሚያካሂደው አድማስ ዩኒቨርሲቲ፤
የዘንድሮውን ጉባኤ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሀርመኒ ሆቴል ያካሂዳል። ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚህ የጥናትና ምርምር ጉባኤ፣ በትምህርት ጥራትና የተማሩ ወጣቶችን ከስራው ኢንዱስትሪ ጋር በሚተሳሰሩበት መንገድ ላይ ያተኮሩ ከ6-8 ያህል የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለውይይት እንደሚቀርቡ የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሞላ ጸጋዬ (ዶ/ር) ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡
‹‹Quality of Education, University linkage and Internalization of Higher Education›› በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ፤ የትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች፣ በርካታ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 748 times