ዘንባባ የማስታወቂያ ድርጅት “ትዝብት ሁለት” የኪነጥበብ ምሽት፣ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቲያትር እንደሚያቀርብ አስታወቀ:: በምሽቱ ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ሠለሞን ተሰማ ጂ፣ ዶ/ር ተሾመ አበራና ቢኒያም መኮንን ዲስኩር እንዲሁም የ”ቦሌ ታይምስ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ደረጀ ይመር “ሽሙጥ ወግ” ያቀርባሉ ተብሏል፡፡በተጨማሪም ግጥምና ሙዚቃ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
መድረኩን የናሁ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ፍቅርተ ተመስገን የምታጋፍር ሲሆን መግቢያው በነፃ መሆኑ ተነግሯል፡፡
Saturday, 31 August 2019 14:15
“ትዝብት ሁለት” የኪነጥበብ ምሽት በብሔራዊ ቲያትር ይቀርባል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና