Print this page
Saturday, 31 August 2019 14:13

ሰምና ወርቅ 21ኛው የኪነ ጥበብ ምሽት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በሰምና ወርቅ ኢንተርቴይመንት በየወሩ የሚዘጋጀው 21ኛው የኪነጥበብ ምሽት የፊታችን ሀሙስ ነሐሴ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
በምሽቱ ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ፣ ሊቀ ጠበብት ዶ/ር ዘሪሁን ሙላቱ፣ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ፣ አርቲስት ዓለማየሁ ታደሰ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ አቶ አዳም ሙሳ፣ ኮሚዲያን ሰመረ ባሪያው፣ ገጣሚያኑ አበረ አያሌው፣ ህሊና ደሳለኝ፣ በቃሉ ሙሉና ማህሌት ታደሰ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ድምፃዊ ዳዊት ዓለማየሁ እንደሚያቀነቅንና የመግቢያ ዋጋ 100 ብር እንደሆነ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው አለሙ አስታውቋል፡፡

Read 6092 times