በታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ የተፃፈው “የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ሃረግ ምንጭ” የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡ እናት የማስታወቂያ ድርጅት ከጐተ ኢንስቲትዩትና ከወመዘክር ጋር ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የመነሻ ሃሳብ የሚያቀርቡት ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ሲሆኑ ፍላጐት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ተጋብዟል፡፡