Print this page
Saturday, 31 August 2019 12:39

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ነገ በእስራኤል ጉብኝት ያደርጋሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ (እሁድ) በእስራኤል ጉብኝት እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምበሲ በድረገፁ እንዳስታወቀው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ እስራኤል የሚያቀኑት በሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንያሚን ኔትኒያሁ ግብዣ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ በእስራኤል ቆይታቸው ከጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትኒያሁ እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ሪውቨን ሪቭሊኒን ጋር እንደማወያዩ፣ በውይይታቸውም የእስራኤልና የኢትዮጵያ ግንኑነትን በሚያዳብሩ ጉዳዮች ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሏል- ኤምባሲው፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ በናዚ በግፍ የተጨፈጨፉ አይሁዶች መታሰቢያ ሃውልት የሆነውን ያድቫቬም የተባለውን ታሪካዊ ቦታ እና ውልት ይገበኛሉ ተብሏል፡፡

Read 991 times