Saturday, 24 August 2019 14:47

‹‹የአዕምሮ ፈውስ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በወይዘሮ ፍቅርተ ደምሴ የተሰናዳውና በግል ሕይወታቸው ዙሪያ የሚያጠነጥነው ‹‹የአዕምሮ ፈውስ›› የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ ከወ/ሮ ፍቅርተ የልጅነትና የትምህርት ቤት ትዝታ ጀምሮ ከአገር ቤት በስደት እስከሄዱበት እንዲሁም በአገረ አሜሪካ ያሳለፉትን ሕይወት የሚያስቀኝ ነው ተብሏል፡፡ እሳቸው ከአለማዊ ሕይወት ተላቀቅኩ እስከሚሉበት የመንፈሳዊ ጉዟቸው ድረስ ይተርካል፡፡ በ106 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ100 ብርና በ20 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን፣ ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ተቸግረው ጎዳና ላይ ለወደቁ ወጣት ሴቶችና ሕጻናት እንደሚውልም ታውቋል፡፡

Read 5630 times