Saturday, 24 August 2019 14:45

‹‹ጥንተ ዮን አቃቢያነ ሀገር›› መጽሐፍ የዛሬ ሳምንት ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


            በደራሲ በላይነህ ታደሰ የተጻፈው ‹‹ጥንተ ዮን አቃቢያነ ሀገር›› የተሰኘ መጽሐፍ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ጎንደር ከተማ በሚገኘው
‹‹ቆብ አስጥል›› የባህል አዳራሽ እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ መጽሐፉ በዋናነት በኢትዮጵያዊነት፣ በጥንታዊ እሴቶችና ጥበቦቿ፣ በቋንቋ፣ በስነ ምግባር፣ በባህልና አስተሳሰብ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን በ13 ምዕራፎችና በ270 ገጾች ተቀንብቦ፣ በ151 ብር ከ90 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመጽሐፉን ዳሰሳ ጨምሮ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ለታዳሚው እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 6332 times