የደራሲ ትዕግስት ታፈረ ሞላ የአጭር ልብ ወለዶች ስብስብ የተካተቱበት ‹‹የባስሊቆስ ዕንባ የተሰኘ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ደራሲዋ ቀደም ሲል በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ለንባብ ያበቃቻቸውን ታሪኮች ከአዳዲስ ስራዎቿ ጋር አጣምራ ለህትመት ማብቃቷን በመጽሐፉ ላይ ገልጻለች፡፡
በ220 ገፆች ተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲዋ ከዚህ ቀደም ከሌሎች ደራሲዎች ጋር በጋራ በታተመ መጽሐፍ ላይ ‹‹ሩብ ጉዳይ›› እና ‹‹ሙሉ ሰው›› የተሰኙ ስራዎቿን ለንባብ ማብቃቷ አይዘነጋም፡፡