Saturday, 24 August 2019 14:38

‹‹ዳይቭ ኮሌክሽን›› የፋሽን ትርዒት የፊታችን ቅዳሜ ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ‹‹የሚስቲካል›› (Miss Tcal) የፋሽን ኩባንያ መስራችና ስራ አስኪያጅ በሆነችው ጽዮን ባህሩ የተዘጋጁ የፋሽን ዲዛይኖች ለእይታ የሚቀርቡበት
‹‹ዳይቭ ኮሌክሽን›› የተሰኘ የፋሽን ትርዒት የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በኤሮስ ሬስቶራንት እንደሚቀርብ ተጠቆመ፡፡ በዕለቱ ዲዛይነሯ የሰራቻቸው የ17ኛው መቶ ክ/ዘመን የአውሮፓ ንጉሳዊያንን የአለባበስ ዘይቤና የኢትዮጵያውያን ካባዎች አጣምሮ በያዘው በዚህ መርሃ ግብር፤ ከፋሽን ትርዒት በተጨማሪ የዳንስና የስዕል አውደ ርዕይ ይቀርባል፡፡ ሰዓሊያን ትርዒቱን ከመድረክ በቀጥታ የሚስሉበትና ሌሎችም አዝናኝ ፕሮግራሞች መሰናዳታቸውን ታውቋል፡፡

Read 752 times