Saturday, 24 August 2019 13:28

ኢትዮ አዲስ እንቁጣጣሽ ባዛር ትላንት ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ታላላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣ ባዛርና ኤግዚቢሽኖችን በስኬት በማዘጋጀት የሚታወቀው ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ያዘጋጀው “ኢትዮ አዲስ እንቁጣጣሽ ባዛር” ትላንት በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት ተከፈተ፡፡
በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ አገር የንግድ ድርጅቶች በተሳተፉበት በዚህ ባዛር ላይ ለሽያጭ የተዘጋጁ ድንኳኖች ተሸጠው ማለቃቸውንና ባዛሩ ጆርካ ከዚህ በፊት ከሰራቸው ባዛሮች በተሳታፊ ቁጥርም ሆነ በጐብኚ ብዛት የተሻለ እንደሚሆን አዘጋጆች ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር አስታውቋል፡፡
ከትላንት ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 6 በሚካሄደው ባዛር ላይ አንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን በየቀኑ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ከድምፃዊያኑ መካከል ሚካኤል በላይነህ፣ ፀጋዬ እሸቱ፣ ዳዊት መለሰ፣ ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ፣ ያሬድ ነጉና በርካታ ወጣት ድምፃዊያን ይገኙበታል ተብሏል::
በባዛሩ መጪውን የትምህርት ዘመን ምክንያት በማድረግ፣ ሁሉም አይነት የትምህርት ቁሳቁሶች በብዛትና በጥራት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡ ሲሆን ሌሎችም የተለያዩ ምርቶች ለገበያ እንደቀረቡ ጆርካ አስታውቋል፡፡
በተንጣለለው የሚሊኒየም አዳራሽ ለልጆች ራሱን የታለ ኮርነር ተዘጋድቷል፤ የተለያዩ መጫወቻዎች፣ ስኬት ቦርድና መንሸራተቻዎች የተዘጋጁ ሲሆን፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው መዝናናት፣ መጐብኘትና መገብየት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታም መፈጠሩን አዘጋጆቹ ገልፀዋል:: ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትም ለበጐ አድራጐት ድርጅቶች የተለያዩ ድንኳኖችን በመፍቀድ፣ ስራቸውን እንዲያስተዋውቁና ከተሳታፊው ድጋፍ እንዲሰበስቡ ማድረጉን ገልፆ፤ በቀጣይም የ2012 የገናና የፋሲካ ባዛሮችን ጨምሮ የ2013 የእንቁጣጣሽን ባዛር በዚሁ በሚሊኒየም አዳራሽ ለማዘጋጀት የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

Read 759 times