Saturday, 17 August 2019 14:28

የዘላለም ጥግ

Written by 
Rate this item
(8 votes)

 (ስለ ሞትና ውልደት)

• ሞት እንደ ውልደት ሁሉ የተፈጥሮ ምስጢር ነው፡፡
ማርክስ አዩሬሊዩ
• ከሞትክ በኋላ ከውልደትህ በፊት የነበርከውን ትሆናለህ፡፡
አርተር ሾፐንሃወር
• ውልደት የሞት መጀመሪያ ነው፡፡ ቶማስ ፉለር
• የውልደት ቀንህ፤ ወደ ሞትም ወደ ሕይወትም ይመራሃል፡፡
ሚሼል ደ ሞንታዥ
• ለሰዎች ማልቀስ ያለብን ሲወለዱ እንጂ ሲሞቱ አይደለም፡፡
ቻርለስ ደ ሞንቴስኪው
• ሕይወት ተቃራኒ የለውም፡፡ የሞት ተቃራኒ ውልደት ነው፡፡ ሕይወት ዘላለማዊ ነው፡፡
ኢክሃርት ቶሌ
• ሕይወታቸውን በጥልቀት የሚኖሩ ሰዎች፤ የሞት ፍርሃት የለባቸውም፡፡
አናይስ ኒን
• ሁሉም መንግስተ ሰማያት መግባት ይፈልጋል፤ ማንም ግን መሞት አይፈልግም፡፡
ያልታወቀ ሰው
• ሞት፤ ለወጣት የሩቅ አሉባልታ ነው፡፡
አንድሪው ኤ.ሩኔይ
• በእያንዳንዱ ማታ፣ ወደ መኝታዬ ስሄድ እሞታለሁ፤ ከእንቅልፌ ስነቃ ዳግም እወለዳለሁ፡፡
ማሃትማ ጋንዲ
• ትርጉም የለሽ ሕይወት ከመኖር ይልቅ፣ ትርጉም ያለው ሞትን እመርጣለሁ፡፡
ኮራዞን አኩይኖ
• ሕይወትን አጣጥም፡፡ ለመሞት በቂ ጊዜ አለ፡፡
ሃንስ ክሪስትያን አንደርሰን
• መሞት ቀላል ነው፤ አስቸጋሪው መኖር ነው፡፡
ፍሬድሪክ ሌንዝ
• ሞት ቅጣት ሳይሆን ሕግ ነው፡፡
ዣን ዱቦስ

Read 3607 times