Saturday, 17 August 2019 14:27

ከአዋቂዎች አንደበት

Written by 
Rate this item
(1 Vote)


• ኢሕአዴግን ማፍረስ አገር ማፍረስ ከሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡… ለሀገር ስንል ስሱ መሆን አለብን፡፡
አቶ የሺዋስ አሰፋ (የኢዜማ ሊ/መንበር)
• --የትግራይ ሕዝብ መገንጠል አይፈልግም፤ ከማን ነው የሚገነጠለው? ፍላጎቱ የህወሐት ነው፡፡---
ሙሉጌታ አረጋዊ (የሕግ መምህር- ለኢትዮ ታይምስ)
• የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወቀስበት ነገር ካለ፣ መከራን ፀጥ ብሎ የሚሸከምበት ጀርባ ጽናቱ ነው… ያ ነው መወቀስም መፈተሽም ያለበት፡፡
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ (የሕግ ምሁር-ለኢሳት)
• … የአባቶቻችን ደም ውስጣችን አለ፤ ዛሬ በአሜሪካን አገርና በአውሮፓ፣ ሌላው አፍሪካዊ አቀርቅሮ ሲሄድ ኢትዮጵያውያን ቀና ብለው የሚሄዱት፣ ያ ደም በውስጣቸው ስላለ ነው፡፡ አድዋ ላይ ድል
የሰራ ደም ነው፤ እያንዳንዱን የሚያፀና ደም::…
መምህር ዘነበ (አንዳፍታ ዩቲዩብ)
• …ቃል ጉልበት አለው፤ይተክላል፣ ይነቅላል:: ትውልድ ይፈጥራል፣ ትውልድ ያጠፋል:: ፍቅር ይዘራል፣ ጥላቻን ይዘራል፡፡ በቃል ውስጥ ብዙ መማር ብቻ ሳይሆን አገር መስራት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ የተሰራችውም የፈረሰችውም በቃል ነው፡፡…
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ  (በ‹‹ማይንድሴት›› መድረክ)
• …መንጋና መንግስት ናቸው ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገባው፡፡ በዓለም ላይ ሰፊ የህይወት ጥፋት የፈፀሙት መንግስትና መንጋ ናቸው፡፡
ዶ/ር ኤርሴዶ ለንደቦ (አንዳፍታ ዩቲዩብ)
• … ምርጫን በተመለከተ እንደ ኢዜማ የተዘጋጀ ፓርቲ ያለ አይመስለኝም፡፡ ነገ ቢካሄድ 400 ወረዳዎች ላይ እጩ ማቅረብ ይችላል፤ ታዛቢ አለው፤ ሁሉ ነገር አለው:: 16 የፖሊሲ ሰነዶች ከሳምንት በፊት በምሁራን ያዘጋጀ ፓርቲ ነው። ግን ይሄ ሁሉ ሆኖ፣ ኢዜማ አገርን ነው የሚያስቀድመው::
አገር መኖር፣ መቀጠል አለበት፡፡ ሕዝብ፣ ከዚህ በላይ መሰቃየት የለበትም ብሎ ያስባል፡፡…
አቶ የሺዋስ አሰፋ (የኢዜማ ሊ/መንበር፤ ለአንዳፍታ)
• …በቀና ንግግርና በቀና ሃሳብ ብቻ አገር የትም አይደርስም፡፡ ቀና ንግግር እያወራን፣ ቅን ሃሳብ ባላቸው መሪዎች እየተመራን፣ ሲኦል ልንወርድ እንችላለን፡፡ እሱ ነው እኔ ግድ የሚለኝ፡፡ ፖለቲካው መሬት መያዝ አለበት፡፡--
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ (የሕግ ምሁር፤ ለኢሳት)

Read 4893 times