Saturday, 17 August 2019 14:19

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(16 votes)

 (ስለ መንግስት)

• የአብዛኞቹ መንግስታት መሰረት ፍርሃት ነው፡፡
ጆን አዳምስ
• መንግስታት በገበያው ውስጥ ጣልቃ መግባት የለባቸውም፡፡
ፍራንክ ቫርጎ
• ሕዝብ መንግስትን መፍራት የለበትም፤ መንግስት ነው ሕዝቡን መፍራት ያለበት፡፡
አላን ሙር
• የትኛው ነው ምርጥ መንግስት? ራሳችንን ማስተዳደር የሚያስተምረን፡፡
ጆሃን ዎልፍጋንግ ቮን ጎተ
• መጥፎ መንግስታት ሁሌም ይዋሻሉ፤ እውነቱን መናገር ሃቀኝነትና ድፍረትን ይጠይቃልና፡፡
ሜህሜት ሙራት አይልዳን
• እንድትዋሽ የምትፈልግ ከሆነ፣ መንግስት የሚለውን አምነህ ተቀበል፡፡
ስቲቨን ማጊ
• የማለም ነፃነት፣ በመንግስት ገና አልተወሰደም፡፡
ኦሾ
• ዜጎች ስህተት ውስጥ እንዳይወድቁ መጠበቅ የመንግስት ሥራ አይደለም፤ መንግስት ስህተት ውስጥ እንዳይገባ መጠበቅ የዜጎች ሥራ ነው፡፡
ዳኛ ሮበርት ጃክሰን
• አገሩን የሚወድ ሰው ተግባር፣ አገሩን ከመንግስት መጠበቅ ነው፡፡
ቶማስ ፓይኔ
• መንግስት እኛ ነን፣ እኛ ነን መንግስት ማለት - እናንተ እና እኔ፡፡
ቲዎዶር ሩስቬልት
• ለመንግስት ገንዘብና ሥልጣን መስጠት፣ ለታዳጊ ልጆች ውስኪና የመኪና ቁልፍ እንደ መስጠት ነው፡፡
ፒ.ጄ. ኦ’ሮዩርኬ
• ሁሉም በመንግስት ገበታ ላይ መቅረብ ይፈልጋል፤ ማንም ግን ምግቡን ማሰናዳት አይፈልግም፡፡
ዌርነር ፊንክ
• ሕዝብ እውነቱን ይወቀው፤ ያኔ አገሪቱ ሰላም ትሆናለች፡፡
አብርሃም ሊንከን

Read 4604 times