Saturday, 17 August 2019 14:04

ቬንዙዌላ፤ በ283 ሺህ በመቶ የዋጋ ግሽበት አለምን ትመራለች

Written by 
Rate this item
(8 votes)

 በ2019 የፈረንጆች አመት አማካይ አለማቀፍ የዋጋ ግሽበት 3.6 በመቶ መድረሱን የጠቆመው ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም፤ ቬንዙዌላ ከአለማችን አገራት እጅግ ከፍተኛው የሆነውን የ282 ሺህ 973 በመቶ የዋጋ ግሽበት ማስመዝገቧን ሰሞኑን ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ጊዜ ከአለማችን አገራት ሁለተኛውን እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስመዘገበችው ዚምባቡዌ መሆኗን የጠቆመው የድርጅቱ ሪፖርት፤ በመጋቢት ወር የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት 176 በመቶ ያህል ደርሶ እንደነበር አመልክቷል፡፡
ደቡብ ሱዳን በ56 በመቶ፣ አርጀንቲና በ56 በመቶ፣ ኢራን በ50.4 በመቶ፣ ሱዳን በ48 በመቶ፣ ላይቤሪያ በ23.3 በመቶ፣ ሃይቲ በ18 በመቶ፣ ሴራሊዮን በ17.46 በመቶ፣ አንጎላ በ17 በመቶ የዋጋ ግሽበት እንደ ቅደም ተከተላቸው፣ ከሶስተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውንም ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

Read 2844 times