Saturday, 17 August 2019 13:36

“ትንሳኤ ኪነ-ጥበብ” የመጀመያውን የጥበብ ምሽት ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


         በሳሚ ማስታወቂያና የህትመት ሥራ ድርጅት በየወሩ የሚዘጋጀው “ትንሳኤ ኪነ-ጥበብ” ወርሃዊ የኪነ-ጥበብ ምሽት የመጀመሪያው ዙር የፊታችን አርብ ነሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ በሚኘው ሳሬም ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በእለቱ ግጥም፣ መነባንብ፣ ወግ፣ ዲስኩርና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን፤ እውቅ ከያንያን ለስኬታቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ቤተሰቦቻቸው፤ ጓደኞቻቸውና ወዳጅ ዘዶቻቸው የምስጋናና የስጦታ መስጠት ሥነ - ሥርዓት እንደሚያካሂዱ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
በዕለቱም ጋዜጠኛ አሸብር በቀለ፣ አርቲስት ባዩሽ ዓለማየሁ፣ መላኩ አለማየሁ፣ አርቲስት ናፒ ታዬ፣ ሰዓሊ ተስፋዬና ሌሎችም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ የመግቢያ ዋጋው መቶ ብር ነው ተብሏል፡፡

Read 2992 times