Print this page
Saturday, 17 August 2019 13:34

“ቡሄ በሉ 1” የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በሀብል መልቲ ሚዲያ አዘጋጅነት የሚካሄደው “ቡሄ በሉ 1” የኪነ-ጥበብ ምሽት ከነገ በስቲያ ነሐሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ የኢትዮጵያ የጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ በክብር እንግድነት የሚታደም ሲሆን ገጣሚያኑ ነብይ መኮንን፣ ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ፣ ኤፍሬም ስዩም፣ ፍሬዘር አድማሱ እና በላይ በቀለ ወያ ግጥም፣ መጋቢ ብሉይ አይነኩሉ ጌታነህ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ እና የኪነ-ጥበብ መምህር ዮናስ ሃይሉ ዲስኩር ያቀርባሉ፡፡
በደራሲ አበረ አዳሙ ቅኔ የሚቀርብ ሲሆን፤ በማህበረቅዱሳን የደብረታቦር ዝማሬ እንደሚቀርብና በተጓዥ የቴአትር ቡድን “ዋ ያቺ አድዋ” ትውፊታዊ ድራማ ለእይታ እንደሚበቃ አዘጋጆቹ ገልፀው፣ በገጣሚና ጋዜጠኛ ተፈሪ አለሙ፣ በአርቲስት አለማየሁ ታደሰና በተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወግ እንደሚርብና መድረኩ በጋዜጠኛ ሚካኤል ዓለማየሁ (የእናኑ ልጅ) እንደሚመራም ታውቋል፡፡ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ነው፡፡

Read 853 times