Monday, 19 August 2019 00:00

የ‹ፍሬ አለም› ሽባባው ‹‹ላስብበት›› መጽሐፍ የፊታችን አርብ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


            ላለፉት 15 ዓመታት በሕጻናት፣ በማህበረሰብና በሴቶች አቅም ግንባታ ላይ በርካታ ስራ ስትሰራ የቆየችውና የንግድ ሥራ ፈጣሪ፣ የማህበራዊ ሥርዓቶች ስትራቴጂስትና የሕጻናት የምግብ ተሟጋች የሆነችው የወ/ሮ ፍሬአለም ‹‹ላስብበት›› የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን አርብ ነሀሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል ይመረቃል።
በመፅሐፉ በዋናነት የፀሐፊዋን ሕይወት የሚተርክ ነው የተባለ ሲሆን፣ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ በርካታ ታዳሚዎችና ኪነ-ጥበባዊ ሁነቶች እንደሚቀርቡ የምርቃቱ አስተባባሪ ምዕራፍ ፕሮሞሽን አስታውቋል፡፡ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው ‹‹ልጆች ባሉበት ሁሉ ምግብ ይኑር›› በሚል አቋሟ ይበልጥ ትታወቃለች፡፡

Read 4694 times