Saturday, 17 August 2019 13:27

“በሀገር ፍቅር ጉዞ” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ተዘዋዋሪ የህትመት ገንዘብና በየካቲት የወረቀት ስራዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው “በሀገር ፍቅር ጉዞ” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
በአብዩ ብርሌ (ጌራ) የተፃፈው ይሄው መጽሐፍ የፀሐፊውን የራሳቸውን ታሪክ፣ ገጠመኞቻቸውን አካትቶ ይዟል፡፡ ፀሐፊው ለኤርትራ ነፃነት እንዴት ከኢሳያስ አፈወርቂ ጐን ሆነው ወደ ጦርነት እንደገቡ፣ የአሲንባን ታሪክና በሱማሌ የነበረውን የእስር ቆይታቸውን በውብ አተራረክ አቅርበውበታል ተብሏል፡፡
በ5 ክፍል የተሰናዳው መጽሐፉ በ590 ገጽ የተቀነበበ ሲሆን፤ በ250 ብር ለገበያ መቅረቡና ክብሩ መጽሐፍት መደብር በዋናነነት እያከፋፈለው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡            

Read 1059 times