Saturday, 17 August 2019 13:17

HIV ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ካለባቸውና ቫይረሱ ወደ ልጃቸው እንዳይተላለፍ በተነደፈው ፕሮግራም ታቅፈው ነገር ግን ልጆቻቸው በቫይረሱ ከመያዝ ያልዳ ኑበት ምክንያት ምንድነው? የሚለውን ግርማ አለማየሁ በየነ ፤ሌሊሳ ሴና ዳዲ እና ሶሎሞን ብርሀኑ ሞገስ ጥናት አድርገው BMC Infectious Diseases volume 18,Article number-: 327(2018) በሚል አድራሻ ለንባብ ብለዋል:: የዚህ አምድ አዘጋጅም ይህንን ጠቃሚ የጥናት ውጤት ለአንባቢዎች መረጃ እንዲሆን እነሆ ብላለች፡፡
ባለፈው ሕትመት የPMTCT ፕሮግራም አለም አቀፍ ገጽታ ምን እንደሚመስል የአለም የጤና ድርጅት ካወጣው መረጃ ማስነበባችን ይታወሳል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የPMTCT ፕሮግራም እና የ(ART) አጠቃቀም ተግባራዊ ቢደረግም ልጆች ግን በቫይረሱ መያዛቸው አልቀረም የሚ ለው ርእስ ያሰፈረውን እንመለከታለን፡፡
የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍ ማለት ቫይረሱ በደምዋ ውስጥ ያለባት እናት ስታረግዝ በእርግዝና ወቅት ፤በወሊድ ጊዜ እና ጡት በማጥባተ ወቅት ቫይረሱ ወደልጅዋ ሲተላለፍ የሚገለጽበት ነው:: በዚህ ምክንያት ከ90% በላይ ለሚሆኑ ጨቅላዎች እና ታዳጊዎች እንዲሁም በአለም ላይ ከ10% ለሚሆነው የቫይረስ ስርጭት ምክንያት ነው፡፡ ፀረ ኤችአይቪ (ARV) መድሀኒት በእርግዝና ፤በወሊድ ወቅት እና ጡት በማጥባት ጊዜ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚረዳ ነው፡፡  
በአለምአቀፍ ደረጃ ከ90% በላይ የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው ያላቸው ሕጻናት የሚገኙት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ ምናልባትም እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ 2010/ድረስ በቫይረሱ የሚያዙ አዲስ ልጆች ቁጥር ከ50% በታች ዝቅ ቢልም በ2015/ የተመ ዘገበው ግን አዲስ በቫይረሱ የተያዙት 150‚000/ ሲሆኑ ከእነዚህም 56‚000 የሚሆኑት ከምስራቅ እና ከደቡብ አፍሪካ ነበሩ:: በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ጨምሮ ቫይረሱ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ በተዘረጋው ፕሮግራም ቅድሚያ እንዲያገኙ በእቅድ በተያዙ 21 ሀገራት ውስጥ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሕጻናት በየአመቱ 110.000 መሆናቸውን ጥናቱ ያሳያል፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሕጻናት ቫይረሱ ከእናቶቻቸው የሚተላለፍባቸው ጡት በማጥባት ወቅት እና አብዛኞቹ ደግሞ በተለያየ መንገድ ከእናቶቻቸው የሚተላለፍባቸው ናቸው፡፡     
እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ የአለም የጤና ድርጅት በነደፈው ስልት ተግባራዊ መደረግ የተጀመረው Option B+ የተሰኘው አሰራር በተለይም ለእርጉዝ ሴቶች (CD4)ን የሚተካ እና የሚወሰደው ፀረ ኤችአይቪ (ART) መድሀኒትም ተስማሚ እንዲሆን የሚረዳ ነው፡፡ ስለዚህም በደማቸው የኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸው እርጉዝ እና በጡት ማጥባት ላይ ያሉ እናቶች የሚጠቀሙበት ነው፡፡ ይህ ዘዴ ቫይረሱ ከእናት ወደልጅ መተላለፉን ወደ 2% ዝቅ የሚያደርግ እና ምናልባት በቫይረሱ ወዳልተያዙ የትዳር ጉዋደኞች ቫይረሱ ሙሉ በሙ ሉም እንኩዋን ባይሆንም በአብዛኛው እንዳይተላለፍ ለማድረግ ያግዛል፡፡
ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው እናቶች በእርግዝናቸውም ይሁን ከወለዱ በሁዋላ ART በትክክል ተጠቃሚ በመሆናቸው በአለም ላይ ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ ወደ 1.3 ሚሊ ዮን የሚሆኑ በቫይረሱ በአዲስ ሊያዙ የሚችሉ ህጻናት ከቫይረሱ ነጻ እንዲሆኑ አስችለዋል፡፡    
ምንም እንኩዋን ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ላለባቸው ለእርጉዝ ሴቶች የጸረ ኤችአይቪ መድሀኒት (ART) በአገልግሎት ላይ ቢሆንም የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት ግን ልጆች ጡት መጥባታቸው ካበቃ በሁዋላ ከ18% ከፍ ያለ መሆኑ አነጋጋሪ ነው፡፡ የዚህ ጥናት ዋን አላማም ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚሰራውን ስራ የሚያሰናክለው ምንድነው? የሚለውን ለመለየት ነው እንደ ጥናት አቅራቢዎቹ ገለጻ፡፡ ጥናቱም የተደረገው በአዲስ አበባ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር May, 2017. ሲሆን በጥናቱ የተካተቱትም በደማቸው ውስጥ የኤችአይቪ ቫይረስ ካለባቸው እናቶች የተወለዱ ከ24 ወራት በፊት እድሜ ያላቸው እና በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሕጻናት፤ በሌላም በኩል በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ ካለባቸው እናቶች የተወለዱ እና ከተወለዱ 24 ወር በታች የሆኑ ነገር ግን የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ያልተገኘባቸው ሕጻናት ናቸው:: ለጥናቱ የተመረጡት እናቶችና ልጆች በPMTCT ፕሮግራም ተጠቃሚ ናቸው፡፡
በጥናቱ ተፈትሸው ከተገኙት ምክንያቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በተዘረጋው ፕሮግራም በተገቢው መንገድ አለመሳተፍ ወይንም አለመጠቀም፤
የትዳር ጉዋደኞች (ባሎች)ዝቅተኛ ተሳትፎ፤
የፀረ ኤችአይቪ ART መድሀኒት አወሳሰድ ዝቅተኛ መሆን፤
የግብረስጋ ግንኙነት ሕመም መኖር፤
ያልታቀደ እርግዝና፤
በሰለጠነ ባለሙያና በጤና ተቋም ሳይሆን በቤት ውስጥ ልጅን መውለድ፤
የተወለደውን ልጅ ሌላ ምግብ በመቀላቀል ከስድስት ወር በፊት መመገብ የመሳሰሉት የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዲተላለፍ ምክንያት መሆናቸው በጥናቱ ተጠቁሞአል፡፡
ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011/ የምትሰራው Option A በተባለው አሰራር የነበረ ሲሆን የአለም የጤና ድርጅት የፈጠረውን አዲስ አሰራር Option B+ በ2012/ተቀብላ በመላው የጤና ተቋማት የPMTCT ፕሮግራም በመተግበር ላይ ትገኛለች፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አሰራር ቫይረሱ በደማቸው ካለባቸው ከአስር እርጉዝ ሴቶች ሰባቱን ቫይረሱ ከእናት ወደልጅ እንዳይ ተላለፍ ለማድረግ ART እንዲወስዱ ቢያስችልም አሁንም የመተላለፍ እድሉ ጡት ማጥባት ካበቃ በሁዋላ እስከ 18% ከፍ ያለ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡
ምንም እንኩዋን ከእናት ወደ ልጅ በመተላለፍ በቫይረሱ የሚያዙ ጨቅላዎች በ65% ቀንሶአል ቢባልም በኢትዮጵያ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2009-2014 ባለው ጊዜ 4800 የሚሆኑ ጨቅላዎች አዲስ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መገኘቱ ተመዝግቦአል:: በጎንደር ፤ጅማ እና ድሬ ደዋ በተደረገው ጥናት በሆስፒታሎቹ ባሉት የPMTCT ክሊኒኮች የቀረቡ መረጃዎች እንደ ሚያሳዩት ከሆነ ከ10-17% የሚሆኑ ጨቅላዎች ከእናቶቻቸው የኤችአይቪ ቫይረስ የተጋባባቸው ሆነዋል፡፡ በአዲስ አበባም በተደረገ ጥናት እንደተመለከተው 8.4% የሚሆኑ ጨቅላዎች ለቫይ ረሱ ተጋላጭ ሆነዋል፡፡
የኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ከ(2013-2015) ተግባራዊ የሚሆን እቅድ ነድፎ ፀረ ኤችአይቪ (ART) ወደ 90% ለሚሆኑ በደማቸው ቫይረሱ ላለባቸው እናቶች እና ቫይረሱ ወደ ጨቅላዎቹ እንዳይተላለፍ ለመከላከል ARV prophylaxis 90% ለሚሆኑ ሕጻናት በመሰጠቱ ስርጭቱን በ2015 ከ5% በታች እንዲወርድ አስችሎአል፡፡ቢሆንም ግን June 2014 12.8% በደማቸው ካለባቸው እናቶች የተወለዱ ጨቅላዎች ቫይረሱ በደማቸው ተገኝቶአል፡፡
በስተመጨረተሻም ግርማ አለማየሁ በየነ፤ ሌሊሳ ሴና ዳዲ እና ሶሎሞን ብርሀኑ ሞገስ በጥናታቸው የሚከተሉትን መፍትሔዎች ጠቁመዋል፡፡  
የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድ ረግ ወንዶች ከሚስቶቻቸው ጋር ተባብረው ስለልጃቸውም ሆነ ስለ ባለቤታቸው እንዲሁም ስለእራሳቸው ጤና ክት ትል በማድረጉ ረገድ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
እናቶች በተለይም ጨቅላ ልጆቻቸውን በምን መንገድ መመገብ እንደሚገባቸው ተገቢው እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ ስለሚረዳ በተገቢው መንገድ የምክር አገልግሎት ማግኘት ይገባቸዋል፡፡


Read 9729 times