Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 09 June 2012 10:49

“ካልተከባበርን የነገ ኢትዮጵያ የለችም”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ጥቁር ሰው” የሚለው አልበም ጠይም በሆነ ቴዲ ወይም ነጭም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማለት የኖህ፣ የሴም፣ የያፌት፣ የካም ዘር አንድ ላይ ሆነው የፈጠሩት የመጀመሪያው ትውልድ የኢትዮጵያ ህዝብ እዚያ አሉ ማለት የአለም ህዝብ አሉ ማለት ነው፡፡ በዚህ በተቀደሰ መሬት ላይ ስናወራ በእውነት ለመናገር ሁላችንም ደካሞች ነን፡፡ አይደለም እንዴ? ምንጊዜም የሚበረታው በእኔ አፍ የማይጠራው እግዚአብሔር ነው፡፡ አንድ የማረጋግጥላችሁ ነገር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን መውደድ ሁሉንም መውደድ ነው፤ ለእኔ ስለምወዳችሁ ስለማከብራችሁ “ጥቁር ሰው” በሚለው አልበም ውስጥ ከተካተቱት አብዛኞቹ ዘፈኖች በብዛት ስለ ታሪካችን፣ ስለማንነታችን፣ ስለማህበራዊ ህይወታችንና ስላለፈውና ስለቀጣይ ህይወታችን እንዲያወሩ የተቻለንን ሁሉ እንካፈል ብያችኋለሁ፡፡ ምን ጊዜም ጭነት የበዛባት አህያ አካሄዷን ለመወሰን ትቸገራለች፡፡

ባለቤቷ ሲመታት ወዲህ ወዲያ ትላለች… አይደለም እንዴ? ወዲህ ወዲያ እያልኩ እዚህ ጋር ለመድረስ እጅግ ከባድ የሚባል ጊዜ ሳልፍ፤ እጅግ ድቅድቅ የነበረውን ጨለማ ሳልፍ እረዳቴ የነበረው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ አላማዬ አንድ ነው፡፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን አልፎ ሰው ልቤ እንደዚህ ፍቅርን ይፈልጋል፡፡
እዚህ ፊትለፊት እንደዚህ አይነት ልብስ ለብሶ ለመቆም፣ የፀዳ ልብስ ለመልበስ በጣም ቀላል ነው፡፡ የከበደ ህይወት ማለፍ ደግሞ ቀላል ይሆናል ብሎ እስከ መዝፈን ሊያደርስ ይችላል፡፡ እውነት እናገራለሁ እናትና አባቱን የማይወድ የለም ወይ ቅደም ተከተል አለው፤ ፍቅር ሁሉን ሊወድ ይችላል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሀዋርያዎቹ ሁሉ ለይቶ ጴጥሮስን በመውደዱ ለምን አይባልም፤ እራሱን የማይወድ ማንንም አይወድም፤ እራሴን መውደዴን የማረጋግጠው እናንተን መውደዴን ሳረጋግጥ ብቻ ነው፤ እዚህ ጋር የቆምኩት በኩራት ነው እግዚአብሔርን እወዳችኋለሁ፡፡ “ጥቁር ሰው” በሚለው ሙዚቃችን ላይ ዛሬ እንዳየነው አባቶቻችን እንዳስተማሩን ዲነግዴ አፄ ምኒሊክ ኢትዮጵያን ለማስፋፋት በሚያደርጉት ጦርነት ጊዜ ወደ ኦሮሞ ግዛት ዘምተዋል፡፡
ወደ ጉራጌም ወደተለያዩ ግዛቶችም ዘምተዋል፡፡ መሀል ላይ ለመገኘት ሁሉም ጋ መገኘት ያስፈልጋል …
… እስከመጨረሻው እወዳችኋለሁ፤ አቅሜ በፈቀደው ሁሉ እግዜር ይስጥልኝ፡፡ አንድ ነገር እንድናገር ይፈቀድልኝ፡፡ እባካችሁን የኢትዮጵያን የሚቀጥለውን እጣ ለመወሰን፤ የሚቀጥለውን ጊዜ ለመወሰን ካለፈው ጊዜ የተሻለውን ገለጥ ገለጥ አድርገን መውሰድ አለብን፡፡ ያለፈውን ደግሞ እንዳይደገም አድርገን መነጋገር አለብን፡፡ ቴዎድሮስ እዚህ ጋ ለመቆም ሙሉ አይደለም፡፡ ቴዎድሮስ ደካማ ነው፤ ቴዲን እዚህ ጋ ያቆመው የእግዚአብሔር ብርታት ብቻ ነው፡፡
እውነት እናገራለሁ፤ ስለሚቀጥለው ጊዜ ማሰብ ከፈለግን ካለፈው ጊዜ የሚጠቅመውን ወስደን ማረም ያለብንን አርመን … ይሄንን ስል ለእናንተ እንደምለው ለራሴም እያልኩ ነው …
… ፍቅር ያስፈልገናል ትክክል ነው፤ ፍቅር ያሸንፋል ሁልጊዜም ከልቤ ነው የምወዳችሁ፤ እውነቴን ነው የአንዱን ድካም አንዱ ይሸፍናል፤ የአንዱን እኔና እህቴ እኔና ወንድሜ ካልተከባበርን የነገ ኢትዮጵያ የለችም፡፡ … በእውነት እነግራችኋለሁ …
ብልህ ሰው ታናሹንም ይሰማል፤ ምናልባት እናንተ ከታች ሆናችሁ ስለምትሰሙኝ እና እኔ ከላይ ሆኜ ስለምናገር ከሁሉ ተሰሚነት ስላለኝ በዚህ መድረክ ከሁሉ ታናሽና የተዋረድኩት እኔ ነኝ፤ ብልህ ከሆናችሁ እየሰማችሁኝ ነው ማለት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ፍቅር ያሸንፋል፡፡ አሜን! ለመጨረሻ ጊዜ በአክብሮት ጋሽ ተስፋዬን አስፈቅጄ እዚህ ፊልም ላይ የተሳተፋችሁ በሙሉ እንድትኖሩ እፈልጋለሁ፡፡
ኢትዮጵያ አገሬ የአፍሪካ መቀነት
የነፃነት አርማ የሉአላዊነት
ኢትዮጵያ አገሬ የአፍሪካ መቀነት
የነፃነት አርማ የሉአላዊነት
ኑሪ ለዘላለም ቅድስት ኢትዮጵያ …
የሚለውን ዜማ ተጫውቷል
(ቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” ክሊፕ በተመረቀበት ምሽት በሂልተን አዲስ ካደረገው ንግግር የተቀነጨበ)
“ጥቁር ሰው” የሚለው አልበም ጠይም በሆነ ቴዲ ወይም ነጭም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማለት የኖህ፣ የሴም፣ የያፌት፣ የካም ዘር አንድ ላይ ሆነው የፈጠሩት የመጀመሪያው ትውልድ የኢትዮጵያ ህዝብ እዚያ አሉ ማለት የአለም ህዝብ አሉ ማለት ነው፡፡ በዚህ በተቀደሰ መሬት ላይ ስናወራ በእውነት ለመናገር ሁላችንም ደካሞች ነን፡፡ አይደለም እንዴ? ምንጊዜም የሚበረታው በእኔ አፍ የማይጠራው እግዚአብሔር ነው፡፡ አንድ የማረጋግጥላችሁ ነገር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን መውደድ ሁሉንም መውደድ ነው፤ ለእኔ ስለምወዳችሁ ስለማከብራችሁ “ጥቁር ሰው” በሚለው አልበም ውስጥ ከተካተቱት አብዛኞቹ ዘፈኖች በብዛት ስለ ታሪካችን፣ ስለማንነታችን፣ ስለማህበራዊ ህይወታችንና ስላለፈውና ስለቀጣይ ህይወታችን እንዲያወሩ የተቻለንን ሁሉ እንካፈል ብያችኋለሁ፡፡ ምን ጊዜም ጭነት የበዛባት አህያ አካሄዷን ለመወሰን ትቸገራለች፡፡ ባለቤቷ ሲመታት ወዲህ ወዲያ ትላለች… አይደለም እንዴ? ወዲህ ወዲያ እያልኩ እዚህ ጋር ለመድረስ እጅግ ከባድ የሚባል ጊዜ ሳልፍ፤ እጅግ ድቅድቅ የነበረውን ጨለማ ሳልፍ እረዳቴ የነበረው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ አላማዬ አንድ ነው፡፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን አልፎ ሰው ልቤ እንደዚህ ፍቅርን ይፈልጋል፡፡

Read 21295 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 12:08