Saturday, 17 August 2019 12:48

የባሌ ተራራ - የጥንታዊ ሰው መኖሪያ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የሰው ልጅ በተራራማ አካባቢዎች መኖር የጀመረው ከቅርብ አመታት ወዲህ ነው የሚለውን ሳይንሳዊ መላ ምት የሚያፈርስ ነው የተባለ የጥናት ውጤት፣ አለማቀፍ ሚዲያዎችንና ባለሙያዎችን በእጅጉ እያነጋገረ ነው፡፡
የሰው ልጅ በተራራ ላይ ይኖር የነበረው ከ12 ሺህ ዓመታት ወዲህ ነው የሚሉ የምርምር ውጤቶች በስፋት መኖራቸውን የሚያወሱት በጥናቱ የተሳተፉት ፕሮፌሰሮች፤ ለዚህም በአስረጅነት የሚቀርበው በቻይና ሂማሊያ ተራራ ላይ ቲቤታውያን ኖረዋል የሚለው እንደ መጀመሪያ ግኝት ይቆጠር ነበር ብለዋል፡፡
በባሌ ተራራ ላይ ከ31 ሺህ እስከ 47 አመት በፊት ሰዎች በረዶና ቅዝቃዜን ተቋቋመው ይኖሩ ነበር የሚለው ሰሞነኛው የጥናት ውጤት፤ የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነትና ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ይኖሩበት እንደነበር ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው ተብሏል፡፡ የባሌ ተራራ በተደጋጋሚ የሰው ልጅ ይኖርበት የነበረ ቦታ መሆኑን የሚያረጋግጡ ግኝቶች መካተታቸውን ጥናቱን አስመልክቶ የቀረቡ ዘገባዎች አመልክተዋል::
እንስሳትና ሰዎች ይኖሩበት እንደነበር የሚያመላክቱ ቅሪት አካሎች በብዛት በምርምሩ እንደተገኙም ተጠቁሟል፡፡  
ጥንታዊ የሰው ልጅ በዝቅተኛ ቦታዎች (ሞቃታማ) ይኖር ነበር የሚለውን አለማቀፍ ተቀባይነት ያለውን ጥናት የሚያፈርስ ነው የተባለው ይህ የባሌው ግኝት፤ ለኢትዮጵያም ተጨማሪ አለማቀፍ እውቅናን የሚያጎናጽፍ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡  

Read 2383 times