Saturday, 17 August 2019 12:48

መልዕክቶቻችሁ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  ለመጣላትም አገር ያስፈልጋል!!


          በአሁኑ ወቅት የማይነሱ ጥያቄዎች የሉም:: ክልል እንሁን ከሚሉ አንስቶ፣ ህገ መንግስቱ መሻሻል አለበት ብለው ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ ቡድኖች አሉ፡፡ በሌላ በኩል በየአምስት ዓመቱ የምናደርገው ብሔራዊ ምርጫ ጊዜውን ጠብቆ (የመጣ ቢመጣ)፤ ካልተደረገ አገር ይፈርሳል፣ ህገ መንግስት ይጣሳል የሚል ክርክርና ሙግት የሚያቀርቡ ወገኖችም ተፈጥረዋል፡፡ እኔ ደግሞ አንድ ምሁር በኢቢሲ እንዳሉት፤ ከሁሉም በፊት ሰላምና መረጋጋት መፈጠር አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ለመጣላትም አገር ያስፈልጋል!! በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለው የአሸናፊነትና የተሸናፊነት ስሜትም መጥፋት ይገባዋል፡፡ በዜጎች ዘንድ የመተማመንና የመግባባት መንፈስ ሊፈጠርም ይገባዋል፡፡ ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚቻለው አገር ሲኖርና ሲቀጥል መሆኑን መዘንጋት የለብንም:: ምርጫም፣ ሥልጣንም፣ ህገ መንግስትም ---- መጣላትም ጭምር የሚቻለው አገር ሲኖር ነው፡፡ ይሄንን አገራቸው ፈራርሳ በስደት ወደኛ አገር የመጡት ሶርያውያን የበለጠ ያውቁታል፡፡
(ኤልያስ ኬ.)

Read 1091 times