Saturday, 09 June 2012 10:47

“ፈላሻው” ፊልም ትናንት ተመረቀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

“ዱላ ቅብብል” ፊልም ይመረቃል

በግሬት ዋሊያ ፒክቸርስ የተሰራው “ፈላሻው” ፊልም ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ተመረቀ፡፡ የ105 ደቂቃ ርዝመት አለው የተባለውን አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፃፉት አማኑኤል ተስፋዬ እና ዮሴፍ ተሾመ ሲሆኑ እስክንድር አሊ ፕሮዲዩስ አድርጐታል፡፡ሰርቶ ለማጠናቀቅ ስድስት ወራት በፈጀው ፊልም ላይ ሄለን በድሉ፣ ታሪኩ ብርሃኑ፣ ካሳሁን ፍስሃ (ማንዴላ) አማኑኤል ሃብታሙ እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ የፊልሙ ታሪክ በአንድ ለጋብቻ በደረሰ  ቤተ እስራኤላዊ ወጣት ዙርያ የሚያጠነጥን ነው፡፡

ግሬት ዋሊያ ፒክቸርስ “መላክ” የተሰኘ ፊልም አምና ለሕዝብ አቅርቦ በባለሙያዎች እና ተመልካቾች ምርጫ በ“ምርጥ ፊልም” ዘርፍ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በሌላም በኩል ለይኩን እና ጓደኞቹ ፊልም ፕሮዳክሽን፤ ሐብታሙ ጥላሁን ፅፎ ያዘጋጀው “ዱላ ቅብብል” ፊልም ነገ በአዲስ አበባና በክልል ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ በ90 ደቂቃ ፊልሙ ላይ ደራሲና አዘጋጁን ጨምሮ ሌላለም ማናዬ፣ ችሮታው ከልካይ፣ ሜሮን ሕብስቱ፣ ገበያው አበበ፣ ወንድወሠን ምትኩ፣ ብዙአየሁ መኮንን እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡

 

 

 

Read 1129 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 10:49