Saturday, 09 June 2012 10:44

“ሕልመኛዋ እናት” ዛሬ ይመረቃል “መንገድ የጠፋባቸው መንገደኞች” ለንባብ በቃ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ነዋሪነቷን በሀገረ እንግሊዝ ለንደን ከተማ ባደረገችው እታለም እሸቱ የተፃፈው “ሕልመኛዋ እናት” የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ እንደሚመረቅ የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር አስታወቀ፡፡በሐገር ፍቅር ትያትር ቤት ትንሿ አዳራሽ ከጧቱ 3 ሰዓት የሚመረቀው መፅሐፍ 475 ገፆች ያሉት ረዥም ልብወለድ ሲሆን ከምርቃት በኋላ ለገበያ እንደሚበቃ ማወቅ ተችሏል፡፡ በምርቃቱ ላይ የክብር እንግዳ የተደረጉት ደራሲ እና ሃያሲ አስፋው ዳምጤ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርት አጋረደች ጀማነህ ሙያዊ ምልከታቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  በተመሳሳይ ዜና በበቃሉ ተገኘ የተፃፈው “መንገድ የጠፋባቸው መንገደኞች” የተሰኘ ረዥም ልቦለድ መፅሐፍ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ገበያ ላይ የዋለው መፅሐፍ 271 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋው 40 ብር ነው፡፡

 

 

 

Read 997 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 10:49