Print this page
Saturday, 10 August 2019 00:00

‹‹ልቢ ዶ ሕልና? የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የ21 ዓመቷ ወጣት ገጣሚ መዓዛ ብርሃነ የበኩር ስራ የሆነው ‹‹ልቢ ዶ ሕልና?›› (ልብ ወይስ ህሊና) የተሰኘ በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
ወጣቷ በግጥሟ በአፍ መፍቻ ቋንቋዋ በኖረችበትና እድሜ ያላትን የሕይወት ፍልስፍና፣ በአካባቢዋ በዙሪያዋ የምታየውን ሕይወትና መስተጋብሩን በግጥሞቸዋ ለማንፀባረቅ ሞክራለች፡፡
የተለያዩ ሀሳቦች ላይ ያተኮሩ ከ95 በላይ ግጥሞችን የያዘው መጽሐፉ በ121 ገፅ የተቀነበበ ሲሆን በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል መጽሐፉ ቀደም ሲል በመቀሌ መመረቁንና በቅርቡ በአዲስ አበባ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን ገጣሚ መዓዛ ብርሃነ ለአዲስ አድማስ ገልጻለች፡፡

Read 3251 times